Send a Sympathy Card
Tuesday, February 4, 2025
9:00 - 10:00 am (Central time)
አቶ ተሾመ እንዬ ገብረአብ ሀምሌ 12 ቀን 1962 ዓ/ም ከናታቸዉ ወ/ሮ ሐመልማል በቀለና አባታቸዉ አቶ እንዬ ገብረ-አብ በኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ ተወለዱ: :እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የመጀመሪያና መለስተኛ ደረጃ ትምህታቸውን በየካቲ ት 12 ት/ቤት የተከታተሉ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዋቻሞ ሁለተኛ ደረጃ አጠናቀዋል ከዚያም ኑሮቸውን በአዲስ አበባ በማድረግ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በዪኒቲ ዪኒቨርሲቲ በማነጅሜንት መጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን በኃላም በተለያዪ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በአስዳደር ስራ ለረዥም አመታት ገልግለዋል:: አቶ ተሾመ ባለትዳርና የ 3 ልጆች አባት ሲሆኑ ከወ/ሮ ህይወት አዳል ጋር በትዳር ለ 20 አመት ኖረዋል:: ለ 9 እመት ባለቤታቸው ወደ አሜሪካ በመምጣታቸው ምክንያት በኢትዮጵያ በቤተዘመድ ድጋፍ እንደእናትም እንዳባትም ሆነው ልጆቻቸውን አሳድገዋል:: አቶ ተሾመ የእግር ኳስ ጨዋታ ማየትንና ከቤተ-ሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ይወዱ ነበር:: አቶ ተሾመ እንዬ በህክምና ሲረዱ ከቆዪ በኃላ ባደረባቸው ህመም ሐሙስ ጥር 22, 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም አርፈዋል:: አቶ ተሾመ መልካም ባህርይና በቀላሉ ከሰው ተግባብተው ጎደኛ ማፍራት የሚችሉ ሰው ነበሩ:: አቶ ተሾመ መልካም ትዝታዎችን: ለባለቤታቸው ለ ወ/ሮ ህይወት አዳል ለልጆቻቸው እዝራ ናርዶስ እና ኔተን ተሾመ ለእህቶቻቸው ሰናይት እንዬ ሀረገ-ወይን እንዬ በላይነሽ እንዬና ለወንማቸው አሸቱ እንዬ በተጨማሪም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ጥለው አልፈዋል::
Teshome Gebreab was born on July 19, 1970 in Hossaina , Ethiopia to Hamelmal Bekele and Eneye Gebreab .Teshome graduated from unity university in Addis Ababa Ethiopia and received BA in management and worked in different government offices for several years. He was married to hiwot adal and he got Blessed with 3 children. Teshome enjoyed watching soccer ball and spent time with family.He was a dedicated father in raising his children. Teshome departed this life on January 30, 2025 . In addition to his parents,the youngest brother Thomas Gebreab preceded him in death. Teshome leaves to cherish his memory to his wife Hiwot ,loving children Ezra, Nathan and Nardos, His sisters Senait ,Haregewain and Belaynesh and his brother Eshetu.
Tuesday, February 4, 2025
9:00 - 10:00 am (Central time)
Kidane Mehret Ethiopian Orthodox Church
Visitation will begin at 9:00, service will follow at 10:00 am.
Visits: 52
This site is protected by reCAPTCHA and the
Google Privacy Policy and Terms of Service apply.
Service map data © OpenStreetMap contributors